ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1445 ኛው የኢድ አል አድሃ(አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ለታካፉል ኢንሹራንስ እድገት የባለ ድርሻ አካላት ሚና አስፈላጊ መሆኑ ተገልጸ

በሐገራችን Interest Free Finance በተለይም ተካፉል ኢንሹራንስ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚያስፈልግ የግሎባል ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጥበበ ተስፋዬ አሳሰቡ፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ቅዳሜ ግንቦት 17, 2016 በተካሄደው Interested Free Finance Panel ውይይት ላይ ተገኝተው ለባለድርሻ አካለት እንደገለፁት ከሻሪያ አማካሪዎች፣ ከኩባንያዎች፣ ከደንበኞች፣ ከኡለማዎች እንዲሁም ከብሔራዊ ባንክ በመደጋገፍ ላይ ያተኮረ ጥረቶች ክፍለ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል፡፡ አሁን የሐገራችን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ Penetration ደረጃ Conventional ጨምሮ 0.3%-0.5% ከ GDP አንፃር ሲሆን ይሄም ከ1% ያነሰ ነው፡፡ አለም ላይ በአማካኝ ካለው 7% GDP አንፃር ዝቅተኛ ሲሆን ከቅርብ ጎረቤታችን ኬኒያ (4%) እንኳን በጣም ያነሰ ነው ብለዋል፡፡ የታካፉል ኢንሹራንስ ድርሻ ደግሞ ምንም እንኳን በቅርብ ጊዜ ወደ ሥራ የተገባበት ቢሆንም ያለው የገበያ ድርሻ 0.1% ያነሰ በመሆኑ ይሄን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር የ Interest Free Financial Service እሴቶች (values) ሊጠበቅ የሚችለው ሁላችንም ባለድርሻ አካላት (Service delivery Chain) ሙሉውን ከታለመለት አላማ አንፃር ስንተገብረው መሆኑን ገልፀው ከዚህ አንፃር የሸሪያ አማካሪዎች ሚና የጎላ መሆኑን አሳስበዋል፡፡ Financial Inclusion የመንግስት ፖሊሲ መሆኑ እንደ ምቹ ሁኔታ በመውሰድ Takaful እንዲሁም ደግሞ አጠቃላይ Interest Free Finance ያለውን ከፍተኛ ተፈላጊነት ለማሳደግና ያሉብንን Awareness ክፍተቶች በመቅረፍ እድሉን መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በዚሁ መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የብሔራዊ ባንክ Bank Supervision Director አቶ ፍሬዘር አያሌው ባንኩ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ሁሉ ለ Interest Free Finance እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡


የ 5,000,000.00 ብር የካሣ ክፍያ ተፍፀመ
